You are on page 1of 4

ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ

ወቅታዊ የኢትዮጵÁን ሕዝብ ብዛት“ ¾¨<MŃ U×’@ አስመልክቶ


የተዘጋጀ ¾T>Ç=Á መግለጫ

በኢትዮጵያ ፊÈራላዊ ዲVክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት


በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ
ወቅታዊ የኢትዮጵን ሕዝብ ብዛት“ ¾¨<MŃ U×’@ አስመልክቶ የተዘጋጀ ¾T>Ç=Á መግለጫ

እንደሚታወቀው የሕዝብና ቤት ቆጠራ በየአስር ዓመቱ እንዲካሄድ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት ይደነግጋል፡፡ በዚህ መሰረት አገር አቀፍ
የሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን በሀገራቸን የተካሄዱ የህዝብ ቆጠራዎቸን በማቀድ፣ በመምራት በማስተባበርና በማስፈጸም ውጤቶቹ ለህዝብ
ይፋ እንዲሆን አድርጓል፡፡ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲም በሕግ በተሠጠው ስልጣንና ኃላፊነት ትክክለኛ፣ ወቅታዊና ታዓማኒነት
ያላቸውን የሥነ-ሕዝብ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ መረጃዎችን በአጠቃላይ ቆጠራ እና በናሙና በመሰብሰብ በመተንተንና በማጠናቀር
ለተጠቃሚዎች እያሰራጨ ይገኛል፡፡

ከቆጠራዎቹ የተገኙ መረጃዎች ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ፣ የልማት ዕቅዶችን ለማዘጋጀት፤ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የሚያስችሉ
ቀመሮችን ለማዘጋጀት፣ ለዕቅድ ክትትልና ግምገማ፣ ድህነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ለመቅረጽ፤ ለኢቨስትመንት፣ የምዕተ
ዓመቱን የልማት ግቦች መሳካት ለመከታተል ወዘተ ከፍተኛ ጠቀሜታ እያበረከቱ ነው፡፡

በሀገራችን ሶስት የህዝብና ቤት ቆጠራዎች እ.ኤ.አ. በ1984፣ በ1994 እና በ2007 ዓ.ም ተካሂደዋል፡፡ በቆጠራዎቹ የተሰበሰቡ ዋና ዋና
መረጃዎች የሕዝብ ብዛት ከ›Ñ` ›kõ °eŸ kuK?፣ በጾታ በዕድሜ በገጠርና በከተማ፣ የብሔረሰብና የሀይማኖት ስብጥር (Ethnic and
Religious Distribution)፣ የወሊድ መጠን (fertility Rate)፣ የሞት መጠን (Mortality Rate)፣ የፍልሰት መጠን (Migration Rate)፣ የሥራ
ሥምሪት፣ የትምህርት ሽፋን፣ የቤቶች ዓይነትና ብዛት መረጃዎች ወዘተ ናቸው፡፡ በመሆኑም በተካሄዱት የሕዝብ ቆጠራዎች የተገኘው
የህዝብ ብዛት በጾታ በሰንጠረዥ1 ቀርቧል፡፡ በ1976 (1984) በተደረገው ቆጠራ 42.6 ሚሊዮን ህዝብ ሲሆን በ1987 (1994) 53.5 ሚሊዮን
እንዲሁም በ1999 (2007) 73.8 ሚሊዮን ሆኗል፡፡

ሠንጠረዥ1. የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ባለፉት ሶስት የሕዝብና ቤት ቆጠራዎች፤


ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ወንድ ሴት ድምር
1976 (1984) 21,436,942 21,179,934 42,616,876
1987 (1994) 26,910,698 26,566,567 53,477,265
1999 (2007) 37,217,130 36,533,802 73,750,932
ምንጭ፡- ማ.ስ.ኤ (የሕዝብ ቆጠራ ሪፖርት 1994-2007 እ.ኤ.አ.)

ጥር 30/2007 ዓ.ም
1.1 የሕዝብ ትንበያ /Population Projection/፤

የሕዝብ ብዛት ትንበያ ሳይንሳዊ መርሆዎችን በመከተል አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ ከተካሄደ በኃላ የሚከናወን ስሌት ሲሆን ይህም ሀገራት
ወደፊት ባሉት ዓመታት (ከ30-50 ዓመታት) ሊኖራቸው የሚችለውን የሕዝብ ብዛት የሚያመለክት ነው፡፡

የሀገራችን የወደፊት የህዝብ ብዛት ትንበያ ስሌት የተዘጋጀ ሲሆን ስሌቱ በሚከናወንበት ጊዜ የተለያዩ ግብዐቶችን በመጠቀም ነው፡፡
እነዚህም ከህዝብ ቆጠራ የተገኘ መነሻ የህዝብ ብዛት፣ ከሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናቶችና ከኢንተርሴንሳል ጥናት የተገኙ የውልደትና የሞት
መጠን፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልገሎት፤ የፍልሰት መጠን ወዘተ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ስሌቱ ሲዘጋጅ የተባበሩት መንግስታት የሥነ-ሕዝብ
ተቋም የሚከተለውን የህዝብ ትንበያ የአሰራር ሂደቶችን በመከተል ነው፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የኢትዮጵያን የህዝብ ብዛት ትንበያ መረጃ እ.ኤ.አ. ከ2008-2037 /2000-2029 ዓ.ም/ አዘጋጅቷል፡፡ ይህ
የሕዝብ ትንበያ ትንተና ሲዘጋጅ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የሚኒስቴር መ/ቤቶች፣ ልዩ ልዩ ተቋማት እና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች (NGO) በተጠራው የውይይት መድረክ ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ግብዕቶችን በማሰባሰብ ነው፡፡ በውይይት መድረኩ ላይ
የተሳተፉ ተቋማትና ድርጅቶች፡- CSA, UNFPA, MOFED, USAID, CDC, FUTURE GROUP, Pathfinder International, etc ናቸው፡፡
በመረጃ ትንተና ወቅት የተባበሩት መንግስታት የሥነ-ሕዝብ ፈንድ /UNFPA/ አለምአቀፍ የሥነ-ሕዝብ አማካሪ በመመደብ ጭምር የሥነ-
ሕዝብ ትንበያው የተሳካና ታዐማኒነት ያለው እንዲሆን ከፍተኛ እገዛ አበርክቷል፡፡

ኤጀንሲው የ30 ዓመታት የሕዝብ ትንበያ (ግምት) በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ አዘጋጅቶ ውጤቱን በአውደ ጥናቶችና ሴሚናሮች፣
በህትመት፣ በድረገጽ እና በተለያዩ ሚዲያዎችም ጭምር ለተጠቃሚዎች አሰራጭቷል፡፡ በሰንጠረዥ 2 እንደተመለከተው የሀገራችን የህዝብ
ብዛት እ.ኤ.አ. July 2014 (ሐምሌ 2006 ዓ.ም) 87.9 ሚሊዎን (ሰማንያ ሰባት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን)፣ July 2015 (ሐምሌ 2007 ዓ.ም)
90.0 ሚሊዮን ( ዘጠና ሚሊዎን)፣ እ.ኤ.አ. July 2020 (ሐምሌ 2012 ዓ.ም) 100.8 (አንድ መቶ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን) እንዲሁም እ.ኤ.አ
July 2037 (ሐምሌ 2029 ዓ.ም) 136.7 ሚሊዮን (አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን) ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ሠንጠረዥ2. የሕዝብ ብዛት ትንበያ አገር አቀፍ እ.ኤ.አ በመካከለኛ ug=I (‘000) (2008-2037)
ሐምሌ 1, ¯.U // July 1, እ.ኤ.አ ¨”É ሴት ድምር
2000 (2008) 38,215 37,504 75,719
2002 (2010) 40,124 39,512 79,634
2006 (2014) 44,204 43,748 87,952
2007 (2015) 45,250 44,825 90,074
2012 (2020) 50,573 50,256 100,829
2017 (2025) 55,939 55,705 111,653
2022 (2030) 61,237 61,081 122,318
2029 (2037) 68,396 68,349 136,92

ጥር 30/2007 ዓ.ም
ምንጭ፡- ማ.ስ.ኤ (የሕዝብ ትንበያ ሪፖርት 2005 ዓ.ም)

1.2 የወሊድ መጠንና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሽፋን - በኢትዮጵያ

ይህ በእንዲህ እንዳለ “በሀገሪቱ ያለው የውልደት መጠን ከሶስትና አራት እጥፍ በላይ የመፈልፍል ያህልና መረን ያጣ አወላለድ” ሳይሆን
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ የሄደ የውልደት መጠን መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በ1992 ዓ.ም አንድ እናት በስነ-ተዋልዶ ዘመኗ 5.5
ወይም 6 ልጆች እንደምትወልድ፤ በ2003 ዓ.ም 4.8፤ በ2006 ዓ.ም 4.1 ልጆች እንደምትወልድ ከሥነሕዝብና ጤና ጥናት የተገኙ መረጃዎች
ያመለክታሉ፡፡ በተጨማሪም ዘመናዊ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሽፋን በ1992 ዓ.ም 6.0 በመቶ የነበረው በ1997 ዓ.ም 14.0 በመቶ፣
በ2003 ዓ.ም 27.0 በመቶ ሲሆን በጥር 2006 ዓ.ም 40.0 መቶ ደርሷል፡፡

ሠንጠረዥ 3፡ የወሊድ መጠንና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሽፋን - በኢትዬጵያ


ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የውልደት መጠን (TFR) ዘመናዊ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት (%)
1992 (2000) 5.5 6.0
1997 (2005) 5.4 14.0
2003 (2011) 4.8 27.0
2006 (2014) 4.1 40.0
ምንጭ፡- የሥነ-ሕዝብና ጤና ጥናት (1992-2006 ዓ.ም)

1.3 የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ሲነጻጻር፤

የኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ከናይጀሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያለ ነው፡፡ በሰንጠረዥ 3 ላይ
እንደተመለከተው የናይጀሪያ የሕዝብ ብዛት በ2003 ዓ.ም (July, 2011) 164.7 ሚሊዮን፣ የሀገራችን ህዝብ ብዛት ሐምሌ 2006 ዓ.ም 87.9
ሚሊዮን ሲሆን የግብጽ ህዝብ ብዛት 87.7 ሚሊዎን ነው፡፡ ሆኖም ግን በህትመት ሚዲያው የተገለጸው “ከሀምሳ አመት ባነሰ ጊዜ አሁን
በህዝብ ብዛት በአፍሪካ እየመራች ያለችውን ናይጀሪያን ከኃላ ለማስከተል ጥድፊያ ላይ ሀገሪቱ እንዳለች” ነው፡፡ ይህ አባባል የሀገሪቱን
የሥነሕዝብ ዕድገት ሁኔታ ያላገናዘበና ወቅታዊ የሀገሮችን የህዝብ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያላስገባና ሙያዊ ግምገማ የሌለው ነው፡፡
የሀገራችን የህዝብ ዕድገት አሁን ባለው የስነ-ህዝብ ባሃሪያት አንጻር ወደፊት የናይጀሪያን የህዝብ ቁጥር የሚበልጥበት ሁኔታ አይታይም፡፡

ሠንጠረዥ 4፡ የኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ከአፍሪካ ሀገሮች ጋር ሲነጻጻር፤


ሀገር ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የህዝብ ብዛት
ናይጀሪያ 2003 (July, 2011) 164,728,579
ኢትዮጵያ 2006 (July, 2014) 87,952,000
ግብጽ 2007 (Dec. 2014) 87,709,269
ምንጭ፡- (CSA-2013, NBS_Nigeria-2013, CAPMAS-Egypt-2014)

1.4 ማጠቃለያ፤

ሕዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚከሰቱ የሥነ-ሕዝብ ባህሪያት (ውልደት፣ ሞትና ፍልሰት) ለውጦች እና በሚመዘገብ የኢኮኖሚና የማህበራዊ
ልማት ዕድገት መጠን በተለይ በጤና፣ በትምህርት ወዘተ ምክንያት ለውጦችን ያሳያል፡፡ በእነዚህ የሥነ-ሕዝብ ለውጥ መስተጋብር
ምክንያቶች የተነሳ ሕዝብ የመጠን፣ የሥርጭት፣ የይዘት / የስብጥር፣ የዕድሜ እና ሌሎች ተዛማጅ ለውጦችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳያል፡፡

የሀገራችንም የሕዝብ ዕድገትም በእነዚህ ምክንያቶች መስተጋብር የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጦችን እያሳየ ነው፡፡ መንግስት የህዝቡን
ዕድገት መሰረት ያደረጉ የልማት ፕሮግራሞችን በመቅረጽና የሥነ-ሕዝብ ፖሊሲን ተግባራዊ በማድረግ ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር
በመስራት ላይ ነው፡፡ በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች (የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ) የጤና አግልገሎት ተደራሽ
በማድረግ የውልደትና የሞት መጠን እንዲቀንስ፣ በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥርና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ሽፋን እንዲጨምር
አድርጓል፡፡ በትምህርት ዘርፍም ተደራሽነቱ የጨመረ ሲሆን ህዝቡ በተለይ ሴቶች ከኢኮኖሚ ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው፡፡
መንግስት የህዝብን ዕድገት መሰረት ያደረጉ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት እያስመዘገበ ያለው ውጤት በግልጽ እየታወቀ የህዝቡን
ነባራዊ ሁኔታን የማይገልጽ በመረጃ ያልተደገፈ የሕትመት ውጤት ማሰራጨት ተገቢ አይደለም፡፡

¾GÑ^‹” ¾Q´w w³ƒ“ ¾¨<MŃ U×’@ uT>SKŸƒ u}sT‹” udÔd© ²È u}"H@Æ Ø“„‹ ¾}[ÒÑÖ< J’¨< እÁK< የኢትዮጵያን
ህዝብ ብዛት አስመልክቶ በአንዳንድ የሕትመት ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መልዕክት ትክክል አይደለም፡፡ u}KÃU ¾— –_e Ò²?×
IÇ` 21 k” 2®®7 ¯.U °ƒS< pê 4 lØ` 141 dU”ታ© °ƒS< ¾¨×¨< QƒSƒ “ የሀገሪቱ የሕዝብ መጠን መረን የለሽና አስደንጋጭ
የተሰኘ፣ ሀገሪቱ በአስፈሪ የህዝብ መጠን ትዋጣለች፣ ከሀምሳ ዓመት በ%Eላ ናይጀሪያን እንደምትበልጥ፣ በሀገሪቱ ያለው የውልደት መጠን
ከሶስትና አራት እጥፍ በላይ የመፈልፍል ያህልና መረን ያጣ አወላለድ በመሆኑ ቀጣዩ ትውልድ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ በላይ
ፖለቲካዊ መቅሰፍት ምፅዓት ነጋሪ ዳፋ እንደሚያገኘው በመግለጽ መንግስት ለሕዝብ ዕድገቱ ትኩረት እንደማይሰጠው“ ይገልጻል፡፡
በህትመት ሚዲያው የተላለፈው መልዕክት የሀገሪቱን ወቅታዊ የህዝብ w³ƒ“ ¾¨<MŃ U×’@ አስመልክቶ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ›?Δc=
ለሕዝብ፣ ለመንግስትና ለዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም በሕዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን የተሰራጩትን ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃዎችን

ጥር 30/2007 ዓ.ም
ያላገናዘu ከመሆኑም በላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ የማይገልጽና መንግስት በሥነ-ሕዝብ °Éу Là እ¾c^ ÁK¨<” ¨<Ö?ታT Y^­‹”
ÁLÑ“²u ’¨<::

በመጨረሻም ኤጀንሲው የሀገሪቱን ወቅታዊ የሕዝብ ብዛትና ተዛማጅ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ለማሰገኘትና የመረጃ ክፍተቶችን
ለማስወገድ 4ኛውን የህዝብና ቤት ቆጠራ በ2010 ዓ.ም ለማካሄድ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ


K}ÚT] Tw^]Á
›„ ›dMð¨< ›u^ ¾Y’ Q´w“ zÃታM eታ+. ²`õ }/U/ª“ ÇÃ_¡}`
eM¡ lØ` 09 33 32 08 39
›„ dIK< ØLG<” ¾Y’ Q´w e +. ÇÃ_¡„_ƒ ÇÃ_¡}` eM¡ lØ` 09 11 71 96
52
›„ dò ÑSÇ= ¾Q´w Ó”–<’ƒ“ S[Í Y`߃ ÇÃ_¡„_ƒ ÇÃ_¡}` eM¡ lØ`
09 11 54 95 37

ጥር 30/2007 ዓ.ም

You might also like